ሥጋ የለበሰው እሳት
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተጸነሰባት ለዚያች ሰዐት ለዚያች ቀን ምስጋና ይገባታል። ኢዮብ መከራ በገጠመው ጊዜ የተወለደበትን ቀን ረገመ፤ “ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም ወንድ ልጅ ተጸነሰ የተባለበት ሌሊት። ያ ቀን ጨለማ ይሁን እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ ብርሃንም አይብራበት” ኢዮ. 3፥3 አለ። እኛ ደግሞ ደስታችን ለጀመረባት ለዚህች ቀን ምስጋና እናቀርብላታለን። ድንግል በድንግልና ሳለች ለፀነሰችበት ለዚህ ቀን አንክሮ […]







