Uncategorized

እሱ ግን ከተናገረው አንዱንም ሳያስቀር ተነሳሣ!

“ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን አነሣዋለሁ” ዮሐ. 2፥19 አላለም ነበር?እንደተናገረ ቤተ መቅደስ የተባለ ሰውነቱን አስነሥቶ አሳየን። “እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ነፍሴን ከእኔ ማንም አይወስዳትም ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ስልጣንአለኝ” ዮሐ. 10፥18 ያለውን ቃሉን ሊፈጽም ጌታ ተነሣ። በዚያ ቦታ ተገኝተው መቃብሩ ባዶ ሆኖ ያዩት ሴቶች እንዴት የታደሉ ናቸው? “መልአኩ አይዟችሁ አትፍሩ” ብሎ አጽናናቸው፤ መቃብሩ ባዶ […]

እሱ ግን ከተናገረው አንዱንም ሳያስቀር ተነሳሣ! Read More »

ገማልያል እና ኒቆዲሞስ

ከአይሁድ ሊቃውንት መካከል ስሙ ገናና ሆኖ የምናገኘው ፈሪሳዊ በሸንጎው መካከል ቢናገር የሚደመጥ ምሁረ ኦሪት ሌዋዊ ማነው ቢባል ገማልያል ከማለት ፈቀቅ እንዳንል የሚያስገድደን በዘመነ ሐዋርያት መግቢያ ላይ የተመዘገቡ ታሪኮችን ስንመለከት ነው። ቅዱስ መጽሐፍ “በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል” ሐዋርያት ሥራ. 5፥34 ብሎ የሚጠራው ይህ ታላቅ ሰው ከታወቁት ሐዋርያት መካከል ቅዱስ ጳውሎስን፣ እስጢፋኖስንና በርናባስን እንዳስተማረ

ገማልያል እና ኒቆዲሞስ Read More »

ዛሬ የዓመቱ መጨረሻ አይደለም!

የመጨረሻው ጫፍ ላይ ስንደርስ የማንከፋው የታክሲ ሰልፍ ላይ ብቻ ይመስለኛል። ምናልባት ሌላም ሊኖር ይችላል።የዓመቱ መጨረሻ ቀን ላይ መሆን ደግሞ እንደ እኔ በዓመቱ መጀመሪያ ቀን ላይ ሆኖ ብዙ ለመሥራት ለራሱም ለሌሎችም ቃል ገብቶ ላልፈጸመ ሰው ከምንም በላይ አስደንጋጭ ነው። ዛሬ የመጨረሻው ጫፍ ላይ ከመድረሳችን በፊት የመጀመሪያው ጫፍ ላይ ሆነን በዚህ ዓመት ብዙ መሥራት አስበን ከነበረ ምን

ዛሬ የዓመቱ መጨረሻ አይደለም! Read More »

የነቢያት ትንቢት የተፈጸመው በዚህ ቦታ ነው፤ አንዱ ስለሁሉ የሞተው በዚህ ተራራ ላይ ነው።

ለዓለም ሁሉ ሕይወትን የሚሰጠውን ገደሉት።ታመው ሳሉ የፈወሳቸውን ሰቀሉት፤ “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ብሎ ያዘዛቸውን መስቀል አሸከሙት። እንዴት ያለ ጭካኔ ነው?ለዐርባ ዓመታት በቃዴስ በረሀ ከዓለት የፈለቀ ውኃ ያጠጣቸው እርሱ አልነበረምን?እነሱ ግን ከዕለታት አንድ ቀን “ተጠማሁ” ቢላቸው ሆምጣጤ አጠጡት። በግብፅ ሳሉ ሞት ከፈረዱባቸው የግብፅ ነገሥታት ያዳናቸውን ከጲላጦስ ሞቱን ለመኑለት። ፀሐይ ከሰዎች በለጠ፤ ጨረቃም ፈጣሪውን አወቀ።መላእክት በዐውደ መስቀል ቆመው

የነቢያት ትንቢት የተፈጸመው በዚህ ቦታ ነው፤ አንዱ ስለሁሉ የሞተው በዚህ ተራራ ላይ ነው። Read More »

ዓይነ ከርም(የጉዞ ማስታወሻ ክፍል አንድ)

በተራራማው የኤፍሬም ርስት የምትገኘው ዓይነ ከርም ከቦታው ስፋት የታሪኳ ብዛት ይገርመኛል የካህኑ ዘካርያስ ቤት በዚያ ይገኛል። “በ እግዚአብሔር ፊት ሁለቱም ጻድቃን ነበሩ” የተባለላቸው እነዚያ ቅዱሳን የሚኖሩበት ቅዱስ ተራራ ተሳለምሁት። እመቤታችን እዚህ ቦታ ለመድረስ ሁለት መቶ ሃያ ኪሎ ሜትር ተጉዛለች። ስትመጣ አረጋዊው ዮሴፍ ለንግድ ሩቅ አገር ሂዶ ስለነበር የተከተላት ሰው አልነበረም። መላእክት በቀኝና ግራ አጅበዋት ከናዝሬት

ዓይነ ከርም(የጉዞ ማስታወሻ ክፍል አንድ) Read More »

የአብርሃም ድንኳን(የጉዞ ማስታወሻ ክፍል ሁለት)

የአብርሃም ድንኳን የተተከለው ወዴት ነበር?ርብቃ ለያዕቆብ ታጭታ ስትመጣ ይስሐቅ የጠበቃት ከ እነዚህ ተራሮች በየትኛው ላይ ሆኖ ይሆን? ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን የሄደው በየት በኩል ይሆን?ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ለፈጣሪው መሠዊያ የሠራባት ዘፍ 12፥8 ቤቴል በኋላም ታላቁ መሥዋዕት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሠዋባት ቀራንዮ ዛሬም አለች። በመጽሐፍ “አብርሃም ቤቴልን ወደ ምሥራቅ ጋይን ወደ ምዕራብ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ ወደ ዓዜብም

የአብርሃም ድንኳን(የጉዞ ማስታወሻ ክፍል ሁለት) Read More »

የንጉስ ቀለበት

እግዚአብሔር የሚወደውን ስጦታ ዛሬ ተቀበለ። የማያበድሩት ባለጠጋ፣ የማይሾሙት ንጉስ ነው። ነገር ግን ቸር ነውና ሰውን ከመውደዱ የተነሳ ከሰው ስጦታን ይቀበላል። ሰውም በእግዚአብሔር ካለው መተማመን የተነሳ ከእግዚአብሔር ተቀብሎ ለእግዚአብሔር መባ ያቀርባል። ሕጻናት ከወላጆቻቸው ገንዘብ ተቀብለው ለወላጆቻቸው ስጦታ እንደሚያቀርቡት ያለ ነው። ዛሬ ወደ ቤተ እግዚአብሔር የቀረበችው ስጦታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ጸሐይና ጨረቃ በተፈጠሩ ቀን መላእክት

የንጉስ ቀለበት Read More »

በስእሏ ፊት ስቆም. . .

ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሰማያዊ ንጉሥ የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤቴ ሆይ! መተዳደፍ በበዛበት ዓለም ስኖር ንጽሕናዋን እንዳላሳጣት ነፍሴን በአንቺ ዘንድ አኖራታለሁ፤ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም በላከው ጊዜ ማረፊያ ያደረገው አንቺን ነውና ካንቺ የከበረ ቦታ ለነፍሴ ስለማላገኝላት በአንቺ ዘንድ አኖራታለሁ። የአብ ሙሽራ እመ አምላክ ሆይ! ወደ አንቺ እጆቼን ዘርግቼ ጸሎቴን አደርሳለሁ፤ዓይኖቼን ቀና አድርጌ ልመናዬን አቀርባለሁ፤ “የልብሱን ጫፍ

በስእሏ ፊት ስቆም. . . Read More »

“በቅዳሴ አፉን የፈታው ሕጻን”

በቅዳሴ አፉን የፈታ ሕጻን ይኼውላችሁ። ምስጋናን እየተመገበ ያደገውን ብላቴና ታዩት ዘንድ ኑ! በሕጻናት ልማድ አበ፣ እመ ብሎ አፍን መፍታት የተለመደ ነበር “ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ” ብሎ ንግግሩን የጀመረ የዚህን ሕጻን ነገር ማሰብ ያስደንቃል። ለጌታስ ሁሉ ይቻለዋል “ ከሕጻናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ” ተብሎ ተጽፏልና። ከታናሽነቱ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ያደረበትን ይህንን የጸጋ

“በቅዳሴ አፉን የፈታው ሕጻን” Read More »

እረኛችን

እረኞች በምስጋና የተቀበሉት መልካሙ እረኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ስለ መልካም እረኝነቱ ቤተ ክርስቲያን ታመሰግነዋለች። እንደዚህ ያለ እረኛ የት ይገኛል? ሕዝቡን ይጠብቃቸው ዘንድ ወደ ዓለም በመምጣቱ እረኛችን እንለዋለን እንጂ እንደምናውቃቸው እረኞች ያለ ባሕርይ የለውም። የዚህ ዓለም እረኛ ሲጠብቅ ኖሮ ከተኵላ ቢያድነውም ራሱ አርዶ ይበላዋል። ከሌባ ጠብቆ ቢያድነውም ራሱ ይሸጠዋል። ከበላተኛ የሚጠብቀው ራሱ ሊበላው ነው። ተንከባክቦ የሚያሳድገው

እረኛችን Read More »