Uncategorized

ሥጋ የለበሰው እሳት

አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተጸነሰባት ለዚያች ሰዐት ለዚያች ቀን ምስጋና ይገባታል። ኢዮብ መከራ በገጠመው ጊዜ የተወለደበትን ቀን ረገመ፤ “ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም ወንድ ልጅ ተጸነሰ የተባለበት ሌሊት። ያ ቀን ጨለማ ይሁን እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ ብርሃንም አይብራበት” ኢዮ. 3፥3 አለ። እኛ ደግሞ ደስታችን ለጀመረባት ለዚህች ቀን ምስጋና እናቀርብላታለን። ድንግል በድንግልና ሳለች ለፀነሰችበት ለዚህ ቀን አንክሮ […]

ሥጋ የለበሰው እሳት Read More »

በመንፈስ ቅዱስ ተፀነሰ፣

በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተወለደ። ዛሬ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መወለድን የምታሰጠንን ጥምቀት መሠረተልን። ከእኛ በተወለደ ጊዜ ለማደሪያ የሚሆን ስፍራ አላገኘምና በከብቶች በረት ተወለደ፤ እኛ ግን በጥምቀት ከእሱ ስንወለድ መኖሪያችን በሰማይ ነውና ሰማይ ተከፍቶ አየነው። ትናንት በልደቱ ከሰማይ ወደ ምድር መጣ፤ ዛሬ በጥምቀቱ ሁላችንን ወደ ሰማይ ይዞ ወጣ። በ ኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ ያላችሁ ውድ የጉባኤ ቤታችን አስተባባሪዎች፣

በመንፈስ ቅዱስ ተፀነሰ፣ Read More »

የክርስቶስ መንገድ

ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ከናዝሬት ወደ ዮሐንስ አምላካችን ኢየሱስክርስቶስ ያደረገው ጉዞ አስደናቂው መንገድ ነው። ከልዕልና ወደትሕትና ከሰማይ ወደ ምድር ያደረገውን ጉዞ የሚተረጉም ጉዞ ነውና። በዮርዳኖስ ሀጢአተኞችን ሊያጠምቅ የተሾመ ካህን የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ አለ። ይህንን የሰሙ ሁሉ ሀጢአታቸውን እየተናዘዙ ሊጠመቁ ወደ ዮርዳኖስ መሄድ ከጀመሩ ስድስት ወራት ተቆጥረዋል። የዛሬው የዮርዳኖስ መንገደኛ እስካሁን ሲመጡ ከነበሩ መንገደኞች ይለያል። ወንጅለኛ ነው

የክርስቶስ መንገድ Read More »

የኢየሱስ እናት በዚያ ነበረች

በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ አንዲት አገር ተላከ፤ ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ነው፤ የእግዚአብሔር መልአክ ለዳዊት የተገለጠበት የኦርና አውድማ ያለውም በሌላ ስፍራ ነው 2ሳሙ. 24፥16፤ ለሶምሶን እናት የተገለጠበትም ቦታ ይህ አይደለም መሳ. 13፥3፤ አብርሃም ልጁንይስሐቅን የሠዋበት ቦታ መልአኩ ገብርኤል የተላከባት ከተማ አይደለችም፤ ታዲያ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልአክ ወደዚህች ከተማ ለምን መጣ የሚለኝ ሰው ቢኖር

የኢየሱስ እናት በዚያ ነበረች Read More »

ማነው እንደዚህ ያከበረ?

መንፈሳዊ በዓልን በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ማክበር ሲገባን በማይገባ ሥነ ሥርዓት ስናከብር እናታያለን። ማነው እንዲህያከበረ? በዕለተ ልደቱ ቤተ ልሔምን በዓይነ ልቡናው ያየ፣ እመቤታችን በአብ ዕቅፍ (ዕሪና) ያለውን አካላዊ ቃልን ታቅፋው የተመለከተ ማነው? መላእክት ሲዘምሩ እረኞችም ከመላእክት ጋር ሲያገለግሉ ሲያድሩ ድምጻቸውን የሰማ ማነው?   የእግዚአብሔር ልጅ በምድር፣ የሰው ልጅ በሰማይ የታየበትን የልደቱን ቀን ለሰማያዊ መለኮቱ፣ ለምድራዊ ሰውነቱ

ማነው እንደዚህ ያከበረ? Read More »

የቃል ኪዳኑ ታቦት በሰማይ

“በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት ታየ” ራእ. 11፥19። ቅዱስ ዮሐንስ በራእይ ስላየው ስለዚህ ቃል ልዩ ልዩ ትርጓሜዎችን የሰጡ ሊቃውንት አሉ።ቤተ መቅደሱ ሰው የሆነው እግዚአብሔር ወልድ ነው ያሉ አሉ።በወልድ ሰው መሆን የሰማያዊው አምላክ ለሰው ልጆች መገለጥን የሚያስረዳ መሆኑን በማብራራት ተተርጉሟል። ተርጓሚው መነሻ ያደረገው ጌታ በቅዱስ ወንጌል “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን መልሼ እሠራዋለሁ”

የቃል ኪዳኑ ታቦት በሰማይ Read More »

አንተ እንደምታስበው አይደለም!

ልጁ የሞተችበት አንድ ሰው መጥቶ በክርስቶስ ፊት እየሰገደ ልመናውን አቀረበ። የለመነው ነገር ምን መሰላችሁ? “ልጄ አሁን ሞተች ሂድና አድናት” ማቴ. 9፥18 የሚል ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ልመናውን ተቀብሎ ልጁን ሊያድንለት ወደ ቤት ሲገባ የሚያለቅሱ ሰዎች ዙሪያዋን ከበዋት ቆመዋል፤ “ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ውጡ” ብሎ ተናገረ። እዚያ የነበሩ ሰዎች በሙሉ በክርስቶስም በኢያኢሮስም ሳቁበት፤ የሞተና ያልሞተ ለይቶ የማያውቅ ሰው

አንተ እንደምታስበው አይደለም! Read More »

መፍትሔው ሌላ ነው!

ችግሮች ሁሉ አንድ ዓይነት መፍትሔ ሊኖራቸው አይችልም፤ የችግሮቻችን ምንጭና የችግሮቻችንም ዓይነት ብዙ ሲሆን የችግር መፍቻ መንገዶችም እንዲሁ ብዙ ናቸው። ሌላው ቀርቶ አንድ ዓይነት ችግሮች እንኳን አንድ ዓይነት ማስወገጃ መንገድ ላይኖራቸው ይችላል። የነነዌ ሰዎች እንዲህ የሚያስጨንቅ ነገር እንዴት መጣባቸው?መርከቧን የሚያስጨንቅ ባሕሩን የሚያናውጥ ነፋስ ሳይታሰብ ድንገት ወረደባቸው። መርከቧ መሄድ አልቻለችም፤ አቅጣጫዋን የሚያስቀይር ነፋስ ገጥሟታል።ሰዎቹ ብድግ ቁጭ ከሚያደርገው

መፍትሔው ሌላ ነው! Read More »