የክርስቶስ መንገድ
ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ከናዝሬት ወደ ዮሐንስ አምላካችን ኢየሱስክርስቶስ ያደረገው ጉዞ አስደናቂው መንገድ ነው። ከልዕልና ወደትሕትና ከሰማይ ወደ ምድር ያደረገውን ጉዞ የሚተረጉም ጉዞ ነውና። በዮርዳኖስ ሀጢአተኞችን ሊያጠምቅ የተሾመ ካህን የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ አለ። ይህንን የሰሙ ሁሉ ሀጢአታቸውን እየተናዘዙ ሊጠመቁ ወደ ዮርዳኖስ መሄድ ከጀመሩ ስድስት ወራት ተቆጥረዋል። የዛሬው የዮርዳኖስ መንገደኛ እስካሁን ሲመጡ ከነበሩ መንገደኞች ይለያል። ወንጅለኛ ነው […]





